Skip to main content

ኢትዮጵያ: በሶማሌ ክልል እስር ቤት ዉስጥ የሚፈጸመው ማሰቃየት

ከፍተኛ የመንግስት ባላስልጣናት በማይቋረጥ የመብት ጥሰት ዉስጥ እጃቸው አለበት።

(ናይሮቢ፣ ሰኔ 28 ቀን 2010) የማረሚያ ቤት ሀላፊዎች እና የጸጥታ ሀይሎች በማሰቃያነት በሚታወቀው እና የኦጋዴን

እስር ቤት በመባል በሚጠራው እስር ቤት ዉስጥ ዜጎች በዘፈቀደ ለዓመታት በማሰር ስቃይ እና ድብደባ ተፈጽመውባቸዋል ብሏል ህዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣው ዘገባ።  አድሱ የኢትዮጵያ(Ethiopia) ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተፈጸሙት ዘግናኝ ጥሰቶች ላይ ምርመራ እንዲጀመር በአስቸኳይ ትዕዛዝ መስጠትና የክልሉ የጸጥታ አካላት እና የመንግስት አመራሮችን ተጠያቂ ማድረግ አለባቸው።

 

ድርጅቱ “ልክ እንደ ሞቱት ነን” በሚል ርዕስ ባወጣው ባለ 88 ገጽ ሪፖርት፦  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት በኦጋዴን እስር ቤት የሚፈጸም ማሰቃየት እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች” ዘግናኝ እና ያልተቋረጠ ሰቆቃ፣ ድብደባ፣ ማዋረድ፣ በቂ ያልሆነ የህክምና አገልግሎት፣ በቂ ያልሆነ የቤተሰብ እና የጠበቃ ጉብኝት ይባስ ብሎም አንዳንዴ በቂ ምግብ አለማግኘት በእስር ቤት መፈጸሙን ያትታል። በመብት ጥሰት የታወቁት የሶማሌ ልዩ ፖሊስ እና የማረሚያ ቤቱ የጸጥታ ሀይሎች ይህንን ሰቆቃ እንደ ፈጸሙ ተነግሯል። የሶማሌ ልዩ ፖሊስ ተጠያቂነቱ ለክልሉ ፕሬዚዳንት ለሆኑት አብዲ ኢለይ በመባል ለሚጠሩት ለአቶ አብዲ ሞሃመድ ኦመር ነው። አብዛኛዎቹ ዕስረኞች የተያዙት ከታገደው የኦጋዴን ነጻ ኣውጭ ግምባር ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው ነው። ከታሰሩ በኋላም ብዙዎቹ ክስ አይመሰረትባቸዉም፣ ለፍርድም  አይቀርቡም።

የኦጋዴን ዕስር ቤት ሳተላይት ካርታ፣h ግንቦት 2016 ኢትዮጵያ © CNES 2018 - Airbus DS 2018; Source Google Earth

“አዲሱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ምንስተር ዶ/ር አብይ አህመድ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በዜጎች ላይ ሰቆቃ መፈጸመቸዉን ቢያምኑም ሀገሪቱ ዉስጥ የተንሰራፋዉን የጸጥታ ሀይሎች ዜጎች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ለማስቆም እና ተጠያቂነትን ማስፈን እስከሁን አልቻሉም” ብለዋል በህዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ፌሊክስ ሆርን። አክለዉም “በኦጋዴን እስር ቤት ያለው አሰቃቂ ሁኔታ፣ የክልሉ ፕሬዝዳንት፣ ከፍተኛ የሶማሌ ክልል ባላስልጣናት እንድሁም የሶማሌ ልዩ ፖሊስ ድርጊቶች አፋጣኝ እና ግልጽ ምርመራ ይሻል”  ብለዋል።

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር  ሰኔ 18 ፓርላማ ፊት ቀርበው የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ዜጎች ላይ ሰቆቃ ሲፈጽሙ እንደነበር እስካሁን ከሚታወቀው የመንግስት የክህደት አካሄድ ወጣ ብለው አምነዋል። በኦጋዴን እሰር ቤት ስለሚፈጸመው ግፍ እና በመላው ሀገሪቱ ስፈጻም ለነበረው ግፍ ዙሪያ ተጠያቂነት ስለማስፈን እንዲሁም ግፍ ለተፈጸመባቸው ፍትህ ስለመስጠት ግን አንዳችም ነገር አላሉም።

ሂዩማን ራይትስ ዎች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎችን እና የመንግስት ከፍተኛ ባላስልጣናትን እንዲሁም 70 የቀድሞ እስረኞችን ቃለ-መጠይቅ አድርገዋል።  ከ2011 - 2018 መጀመሪያ በኦጋዴን እስር ቤት ዉስጥ የተመዘገቡትን ግፎችን እንደ ግበኣት ተጠቅመዋል።

 

“ሶስት ዓመት ሙሉ ብቻዬን በጨለማ እስር ቤት ዉስጥ ነበር ያሰሩኝ” ሲሉ ተናግረዋል አንድ የቀድሞ እስረኛ።  “ማታ ማታ ብቻ ሊያሰቃዩኝ ወደ ሆነ ቦታ ይወስዱኝ ነበር። የእስር ቤቱ ሀላፊዎች ብዙ ግፍ ፈጽመውብኛል። በገመድ ወጥረው በማሰር ብልቴን አኮላሽተዋል። በሚጥሚጣ የተሞላ ላስቲክ ዉስጥ አናቴን አስገብተው አቃጥለውኛል። መጮህ እንኳን እንዳልችል አፌ ውስጥ ጨርቅ ይጠቀጥቁ ነበር።”

በመለው እስረኞች ፊት ልብሳቸዉን አስወልቀው እርቃናቸውን እንደ ደበደቧቸው እና ይህንንም የሚያደርጉት በእስረኞች ፊት ለማዋረድ እና ሁሉም እስረኞች እንዲፈሩ ለማድረግ ነበር።” ብለዋል ቃለ-መጠይቅ ያደረግናቸው የቀድሞ እስረኞች።

 

“አንድ ቀን ሁሉም እስረኞች ፊትለፊት ራቁቴን መሬት ላይ ካስተኙኝ በኃላ ጭቃ ዉስጥ እያገለባበጡ  በዱላ ደበደቡኝ” ያለው ምንም ክስ ሳይመስረትበት ለ5 ዓመት የታሰረው የ40 ዓመቱ ሆዳን ነው። “አንድ ጊዜ ደግሞ አንድ ትልቅ ሽማግሌ ሴት ልጁ ፊት ራቁቱን እንዲቆም አድርገዉት ነበር። ይህ ሁሉ መላው እስረኞች እንዲያዩት ተደርጎ ሲፈጸም በጣም ያሳፍራል”

 

እስረኞቹ እንደተናገሩት የማረሚያ ቤቱ ከፍተኛ ሀላፊዎች እና የልዩ ፖሊስ ከፊተኛ አመራሮች በእስር ቤት ዉስጥ የሚፈጸሙትን የማሰቃየት፣ እስረኞችን መድፈር እና ምግብ መከልከል በማዘዝ ብቻ ሳይሆን ራሳቸውም በአከል ተገኝተው ሲፈጽሙ ነበር። በእስረኞች በተጨናነቀው እስር ቤት ዉስጥ የእስር ቤቱ አለቆችም መረጃን በድብደባ ይወስዱ እና ለከፍተኛ ሀላፊዎች ያስታላልፉ ነበር። ከዝያ እስረኞችን ለሌላ ቅጣት ይመለምሉ ነበር።

 

አሳሳቢ የሆነው የእስረኞች መጨናነቅ፣ በእስር ቤት ዉስጥ የሚፈጸሙት ማሰቃየት ፣ የወረርሽን በሽታ ክስተት፣ እጅግ ከፍተኛ የምግብ እና የዉሃ እጥረት እንዲሁም የጤና አገልግሎት እና የንጽህና እጦት ብዙ እስረኞችን ለሞት ዳርጓል።

 

በኦጋዴን እስር ቤት ዉስጥ ብዙ ልጆች ተወልደዋል። አንዳንዶቹ በእስር ቤት ዉስጥ ሴቶች በሚደፈሩበት ወቅት የተጸነሱ ናቸው። ብዙ እናቶች ያለምንም የጤና እርዳታ እና ያለምንም ዉሃ እዝያው እስር ቤት ዉስጥ መውለዳቸዉን ተናግረዋል። 

ቃላ-መጠይቅ የደረግናቸው ሁሉም የቀድሞ እስረኞች ፍርድ ቤት ተወስደው እንደማያዉቁ እና ምንም አይነት ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ተናግረዋል። ሂዩማን ራይትስ ዎች ያነጋገራቸው የቀድሞ ዳኞች ምንም አይነት መረጃ ያልተገኛባቸው እና አንድ ጊዜ እንኳ አይተዋቸው የማያዉቁ እስረኞች ላይ ፍርድ እንዲያስተላልፉ ከፍተኛ የሶማሌ ክልል ባላስልጣናት ጫና ያዳርጉ እንደ ነበር ገልጸዋል።

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰራዊት በ2007/2008 የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ግምባር ላይ በወሰዱበት ወቅት በዘፈቀደ ግድያን፣ ማሰቃየትን፣ መድፈርን ጨምሮ ሌሎች የጦር ወንጀሎችን እና የሰው ዘር ላይ ወንጀል ፈጽመው ነበር። ከዝያ በኃላ የተቋቋመው የሶማሌ ልዩ ፖሊስም በሶማሌ ክልል ዉስጥ በተደጋገሚ ተመሳሳይ ወንጀሎችን በመፈጸም የጅምላ ቅጣቱን አስቀጥለው ነበር። የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ ዘልቆ በመግባት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ገድለዋል። አንድ ሚሊዮን ዜጎችንም ከቄያቸው አፈናቅለዋል።

የፌዴራሉ መንግስት የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስን በእጅጉ ማደስ ወይንም ሙሉ በሙሉ መበተን  እና ከፍተኛ አምራሮቹን ተጠያቂ መድረግ እንዳለበት ብለዋል ሂዩማን ራይትስ ዎች አሳስቧል።

 

ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚፈጸመው ድብደባ እና ስቃይ እጅግ አሳሰቢ ነው። ለሂዩማን ራይትስ ዎች በመደበኛ ሁኔታ እየደረሰው ያለው ሪፖርት  በመላው ሀገሪቱ ዉስጥ መረጃ በማሰቃያት እንደሚወሰድ ያመለክታል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የኦጋዴን እስር ቤት ላይ ብዙ ክትትል አድርገዋል። ነገር ግን የክትትሉ ሪፖርት ለህዝብ እስካሁን በይፋ አልተገለጸም። የሚፈጸሙትን ግፎች በተመለከተ የእርምት እርምጃዎችም ተወስደው ከሆነም ምን አይነት እርምጃ እንደተወሰደ አልተገለጸም።

 

የቆሰሉ እስረኞች፣ ህጻናት እና እርጉዝ ሴቶች ከኮሚሽኑ ጉብኝት አስቀድመው ወይ በድብቅ ቤት ይታሰራሉ አልያም ደግሞ ከማረሚያ ቤቱ ዉጭ እንዲቆዩ ይደረጋሉ ብለዋል የቀድሞ እስረኞች። ሌሎቹ ደግሞ ለኮሚሽኑ ምን አይነት መልስ መመለስ እንዳላባቸው ትዕዛዝ ይሰጠን ነበር ብለዋል። እስር ቤቱ ዉስጥ ያለዉን ሁኔታ ለኮሚሽኑ በግልጽ የተናጉሩት እስረኞች ሰቅጣጭ የበቀል እርምጃ ይጠብቃቸዋል ብለዋል።

 

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር በኦጋዴን እስር ቤት የተፈጸሙትን ሰቆቃ የሚያጣራ እና በሁሉም የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ ሀላፊዎች በእስር ቤቱ ዉስጥ ላደረሱት ግፍ የወንጀል ምርመራ እንዲደረግባቸው የፌዴራል ኮሚሽን ማቋቋም አለባቸው። ይሄው ኮሚሽን አሁን በኦጋዴን እስር ላይ የሚገኙትን እስረኞች ጉዳይ በመገምገም እንዲፈቱ ወይንም በተጨባጭ መስረጃ የተደገፈ ክስ እንዲመሰረትባቸው ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለባቸው።

“በኦጋዴን እስር ቤት እየተፈጸመ ያላው ማሰቃየት እና ግፍ ከሚነገረው በላይ ነው” ብለዋል ሆርን። ዶር አብይ ማሰቃያትን በግልጽ ማውገዛቸውን መቀጠል አለባቸው። በኦጋዴን እስር ቤት ላይ እርምጃ በመዉሰድ ይሄን ሰቆቃ ለማስቆም ያለቸዉን ቁርጠኝነት ማሳየት አለባቸው።

 

የተመረጡ ምስክርነቶች (ሁሉም ስሞች ተቀይረዋል)

የማይቆም የግፍ አዙሪት ላይ የ 28 ዓመቱ አብዱሰላም:

“ሶስት ዓመት ሙሉ ብቻዬን በጨለማ እስር ቤት ዉስጥ ነበር ያሰሩኝ” ብለዋል አንድ የቀድሞ እስረኛ። “ማታ ማታ ብቻ ሊያሰቃዩኝ ወደ ሆነ ቦታ ይወስዱኛል። የእስር ቤቱ ሀላፊዎች ብዙ ግፍ ፈጽመውብኛል። በገመድ ወጥረው በማሰር ብልቴን አኮላሽተዋል። በሚጥሚጣ የተሞላ ላስቲክ ዉስጥ አናቴን አስገብተው አቃጥለውኛል። መጮህ እንኳን እንዳልችል አፌ ውስጥ ጨርቅ ይጠቀጥቁ ነበር. ቀን ቀን ትንሽ ምግብ ይሰጡኛል አንድ ዳቦ እና አልፎ አልፎ ደግሞ ትንሽዬ ወጥ። ሚስቴንም እዚሁ እስር ቤት ውስጥ ደፈሯት። በመደፈሯ የኔ ያልሆን ልጅ ወለደች።”

 

ዉሃን በመጠቀም ሚፈጸ ማሰቀየት፣ የ26 ዓመቷ ፋጡማ፥

አጆቻችንን በገመድ ጠፍረው ካሰሩን በኃላ ከቁመታችንን በሚበልጥ ገንዳ ዉስጥ ይከቱን እና እዛው ያቆዩናል። በአንድ ጊዜ 10 ሰዎችን እዛ ገንዳ ዉስጥ ይጨምራሉ። ጥያቄያቸው ያው የተለመደው “ከኦብነግ ማንን ታውቅያለሽ? እንዴት ነው የረዳሻቸው?...” ይጠይቁናል። እዛ ገንዳ ዉስጥ ከሚከቷቸው ሰዎች መኃል አንዳንዶቹ ከገንዳው ሲያወጧቸው ምንም መልስ አይሰጡም እዛው ዉስጥ የሞቱ ያሉ ይመስለኛል።

 

ግለ-ሂስ የ32 ዓመቱ አሊ

ሲመሽ እስር ቤት ዉስጥ ግለ-ሂስ ይጀመራል። ይሄን የሚያደርጉት እስረኞች ናቸው። ጠዋት ሪፖርቱ ለእስር ቤቱ ዘበኞች ይሰጣል። ብዙ ከካድክ በዙ ትደበደባለህ። በዙ ካማንክ ትንሽ ብቻ ነው የሚትሰቃየው። በግለ-ሂሱ ግዜ ብዙ ካማንክ ብዙ ጥፊ ያርፍብሃል። ለካፖው (የክፍሉ አለቃ) ምንም ነገር ካላመንክ እዛው በእስረኞች ትደበደባለህ።

 

እስረኞችን ልብስ ማስወለቅ እና ማዋረድ፣ የ28 ዓመቱ ሞሃመድ

ብዙ እስረኞችን ራቁታቸውን አይቻለሁ። ዝናባማ እና ጭቃማ ምሽት ነበር። ከየክፍሎቻችን ጠሩን እና ልብሶቻችንን እንድናወልቅ አዘዙን። ከዝያ ጭቃው ዉስጥ አንከባላሉን። አንድ አንዶቻችን ራቁታችን ወደ ክፍላችን ተመለስን። ገሚሶቹ ደግሞ ብልታቸዉን ተያይዘው በሰልፍ ወደያ ክፍላቸው እንዲገቡ አደረጉን። ይሄን ሁሉ ሲያደርጉ ጥበቃዎቹ እየሳቁብን ፎቶ ያነሱን ነበር።

 

ሌሎች እስረኞች ላይ ግፍ ለመፈጸም ያለው ከፍተኛ ጫና፣ የ 31 ዓመቱ አብዲርሃማን፥

አንድ እስረኛ ሌላዉን እንዲያሸማቅቅ ሁሌም ያዙናል። በጣም ዘግናኝ ነገር የተፈጸመው ግን አንድ ቀን ነበር። የተወሰኑ  እስረኞችን አንድ ቦታ ከሰበሰቡ በኃላ አንዱ አንዱ ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንድፈጽም አዘዙዋቸው። ለሁሉም የብረት ዱላን ሰጧቸው። እምቢ ካልኩ እራሴን መግደል እንደሚኖርብኝ ነገሩኝ። እምቢ ካልን ይደበድቡናል። የህሊና ቅጣቱ ግን ሁሌም ከአዕምሯችን አይጠፋም።

እስር ቤት ዉስጥ ስለመዉለድ፣ የ ፫፩ ዓመቷ አያን

እኔ እዛ እስር ቤት በነበርኩበት ወቅት ከተወለዱት ህጻናት ዉስጥ አንዳቸዉም ሙያዊ የጤና እርዳታ አለገኙም። መውለጃዬ ሲቃረብ የጤና እርዳታ እንዲሰጠኝ ጠይቄ ነበር። ከሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ያገኘሁት መልስ ግን እንዲህ የሚል ነበር “ስትፈሊጊ ሽንት ቤት ዉስጥ ወልደሽ ጣይው ልጄን ማላቱ ነው፣ ምንም ዋጋ የለቻዉም። ብያድጉም “የኦብነግ ደጋፊ ነው የሚሆኑት” ለመዉለድ ሆስፕታል እንድወስዱኝም ጠይቄ ነበር። ግን ሳቁብኝ። ጭማሪ ዉሃም ስጠይቃቸው ከለከሉኝ። ስለዚህ እስር ቤት ዉስጥ ወለድኩኝ። ሴቶቹ የተሳሉ ቁራጭ ብረቶች ነበራቸው። በሱ ብረት ነበር እምብርቱን ከኔ ቆርጦ ያሰሩት።

 

በእስር ቤቱ ያለው የፍርሃት ድባብ እና ተደጋገሚ ሞት፣ የ 30 ዓመቱ ሖዳን

በየሌሊቱ እስረኞች ስደበደቡ እሰማለሁ። ብዙ ልቅሶዎችን እሰማለሁ። ጠዋት ለቁርስ ስንገናኝ ማታ እነማን በላፈው ሌሊት እንደተወሰዱ በለሆሳስ ያወራሉ። እነማን በድብደባ መሞታቸዉን፣ እነማን ማታ እንደተደፈሩ፣ እነማን ማታ እንደ ተደበደቡ የወራሉ። በየቀኑ ማታ ተወስዶ ሲደበደቡ እንደ ሞቱ ወይንም በዛው እንደቀሩ እንጠይቃለን። ማን ቀጣይ እላማ እንደሆና እያሰብን በፍርሃት ተሸብባን ነበር የኖርነው።

የኢትዮጵያ ሰብ አዊ መብት ኮሚሽን ጉብኝት፣ የ40 ቷ አሚና

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በሚመጣበት ወቅት ነባሮቹን ያስወጡን እና አዳዲስ እስረኞችን ብቻ ያቀርባሉ። እነሱ ከሚደብቁት ሰዎች መኃል አንዱ ነበርኩኝ። ገርባሳ የሚባል የወታደር ካምፕ ወስደዉኝ ነበር። መጀመሪያ ግዜ ለአንድ ሳምንት ነበር እዛ ያቆዩኝ። አሮጊቶችን ፣ ህጻናትን፣ ፊታቸው የቆሰለዉን፣ አካላቸው የቆሰሉትን የሰብአዊ መብት ኮሚሽኑ እንዳያየቸው ይደብቋቸው ነበር።

Your tax deductible gift can help stop human rights violations and save lives around the world.

Region / Country