Skip to main content

ምስራቅ ኣፍሪካ፥ የተቃዉሞና ሀሳብን የመግለጽ ነጻነጽ አፈና

ለተጠያቅነትን ቅድሚ ይሰጥ፣ የጥቃት ሰለባዎች ይካሱ

(ናይሮቢ ጥር 12፣ 2017) – የምስራቅ አፍሪካ መንግስታት በተቀዉሞ ሰልፈኞችና ሀሳብን በመግለጽ ነጻነት ላይ እየወሰዱ ያለው ጭቆና በአካባቢው የሰብአዊ መብት ሁኔታን እጅግ አሳሳቢ አደጋ ዉስጥ ከቶታል ብሏል ሂዉማን ራይትስ ወች ዛሬ ባወጠው እ.ኤ.አ. የ2017ዓ.ም የአለም ዓቀፍ ሪፖርት።

ኢትዮጵያ አንድሁም በኬንያና በዩጋንዳ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በብዛኛው ሰላማዊ የነበሩ ሰልፈችን ለመበተን አላስፈላጊና ያልተመጣጠነ ሀይል በመጠቀም ለሰዎች ህይወት መጥፋትና አካል ጉዳቶች ምክንያት ሆነዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥ በዚህ ዓመት  በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ተገድለዋል። የምስራቅ ኣፍሪካ መንግስታት በየሃገሮቻቸው ላይ የሚደርስ የ ፖሊሲ ትችትን ለማፈንና የጋዜጠኞችን ስራ ለማደናቀፍ የሀይል እርምጃዎችን መዉሰድ፣ በዘፈቀደ ማሰርና የወንጀል ክሶችን መመስረት ጨምሮ በርካታ ዘዴዎችን ተጠቅመዋል። እነዚህ  የሃገራቱ መንግስታት የጸጥታ ሀይሎች በህዝቡ ላይ ያደረሱትን ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለመመርመርና ኣስፈላጊዉን ቅጣት ለመስጠት ኣልቻሉም። ስደተኞች፣ በተለይም በኬንያ የሚኖሩ ስደተኞችን አስገድዶ የመመለስ ዛቻ ደርሶባቸዋል።

የታጠቁ የመንግስት ወታደሮች በመስከረም ወር 2009 ዓ. ም በቢሾፍቱ ኢትዮጵያ በተከበረው የኢሬቻ በአል ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰዎችን ሲመለከቱ። © 2016 Getty Images


‘’የምስራቅ አፍሪካ መንግስታት ለዜጎቻቸው የሀሳብን የመግለጽ ነጻነት እና የመሰብሰብ መሰረታዊ መብቶች እጅግ አነስተኛ ግምት ነው የሰጠው’’ ብለዋል ሂዩማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ተባባሪ ዳይሬክተር  ማሪያ ቡርኔት። ማሪያ ቡርኔት እንዳሉት ኢትዮጵያ ታይቶ የማይተወቁ ሰልፎችን በጭካኔ ለመጨፍለቅ የውሰደችው እርምጃ ለከባቢው የመጨረሻው ዝቅተኛ ደረጀ መብት ጥበቃ ሆኖ አልፏል።

በባለ 687 ገጹ የዓለም ሪፖርት 27ተኛ እትም ሂውማን ራይትስ ወች ከ90 በላይ በሆኑ ሃገራት ያለውን የሰብዓዊ መብት ትግበራ ገምግሟል። በዚህ የማስተዋወቂያ ጽሁፍ ዋና ዳይሬክተር ኬንዝ ሮዝ አዲስ የህዝባዊ አገዛዝ ትውልዶች የሰብዓዊ መብቶችን ጽንሰ ሃሳብ ለመቀልበስ መሻታቸውን ጽፈዋል፤ መብትን የሚያስተናግዱበት መንገድ የብዙሃንን ፍላጎት ለመገደብ ባመቸ መልኩ መሆኑን ጽሁፋቸው ይገልጻል። ከዓለም ዓቀፉ የምጣኔ ሃብታዊ እድገት ትርፍ ተቋዳሽ እንዳልሆኑ የሚሰማቸው ሰዎች እና እየጨመረ ባለው የብጥብጥ ስጋት የሲቪክ ማህበረሰብ ቡድኖች፣ መገናኛ ብዙሃን እና ህዝቡ መብቶችን የሚያከብር ዴሞክራሲ እንዲገነባ አወንታዊ ሚና መጫወት አለባቸው።

ሙሉ በሙሉ የአከባቢው መንግስታት በጸጥታ ሀይሎቻቸው የደረሱትን በከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ጥቃቶች በየግዜው ለመመርመር አለመፍቀዳቸው ተጎጅዎች እንዳይካሱ መንገድ ዘግቶዋል ብሏል ሂዉማን ራይትስ ወች። በኢትዮጵያ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በመላው ሀገሪቱ የተከሰተዉን የመንግስት ፖሊሲ ተቃዉሞ በሀይል ለመጨፍለቅ በወሰዱት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ተገድለዋል፣ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ በቁጥጥር ሥር አውሏል። በኢሬቻ ክብረ-በዓል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የበዓሉ ተሳታፊዎች ላይ የመንግስት ጸጥታ ሀይሎች የወሰዱትን ርምጃበ ተከትሎ በተነሳ መረጋገጥ መንግስት የአስኳይ ግዜ አዋጅ በማወጅ የዜጎችን መሰረታዊ መብቶች ገድቧዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የሰልፈኞቹን ሞትና የመብት ጥሰቶች በተገቢው መልኩ ለመመርመር አልቻለም።

በኬንያ፣ በሰሜን ምስራቅ ኬንያና ናይሮቢ አከባቢዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት የጸጥታ ሀይሎች ባደረጉት የጸረ-ሽብር እንቅስቃሴ ቢያንስ 34 ሰዎችን በማስገደድ ሰዉሯል። ሁለት ሰዎች ወድያው ቢለቀቁም በአንደኛው ላይ የሽብር ክስ ተመስርቷል። የዩጋንዳ ፖሊሶች እና የመከላከያ ሰራተኞች በምዕራብ ርዌንዞሪ ክልል ተጠርጣርዎችን በቁጥጥር ሥር ለማስገባት በሚል ምክንያት ቢያንስ 13 ሰዎችን ገድሏል።ሶማሊያም በፖሊቲካዊ አመጽ የብዙ ሰላማዊ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል።

በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ቡሩንዲና ሌሎች ሀገሮች ዉስጥ በተከሰቱት ግጭቶችና ክሶች ምክንያት የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች የተለያየ ተጽእኖ የተፈጠረባቸውን በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን አስተናግደዋል። ዩጋንዳ ስደተኞቹን ለማዋሃድ ስትጥር፣ ኬንያ መንግስት ደግሞ ተስማምቶ የፈረመዉን የአለም ዓቀፉን የስደተኞች ህግ በመጣስ የሶማሊያ ስደተኞች የተጠለሉበትን ዳዳብ የተባለውን የስደተኞች ካምፕ ለመዝጋት አስታወቋል። ይሄ ዉሳኔ በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሌ ስደተኞች ወደ መጡበት የጦርነት ቀጠና አንዲመለሱ ያስገደደ ሲሆን የቀሩትም ስለ ደህንነታቸው እና እጣፈንታቸው እየፈሩ በስጋት አንዚኖሩ ሆነዋል።

በመላው ምስራቅ ኣፍሪካ የሚገኙ ሀገራት ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን  ላይ ያነጣጠረና በመንግስት የተቀናባበሩ ማስፈራሪያዎችና ጥቃቶች አሁንም በስፋት ይስተዋላል። በኤርትራ ውስጥ እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 2001ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ገለልተኛ ጋዜጠኞች ለየብቻ እስር ቤት ዉስጥ ታስረው ይገኛሉ።  ከእነዚህ እስረኞች ውስጥ አንዳቸዉም ፍርድ ቤት አልቀረቡም። አንድም ነጻ ጋዜጣ አንድሰረ ኣልተፈቀደም። ኢትዮጵያም በርካታ ጋዜጠኞችን እናና ጦማሪዎችን የጸረ-ሽብር ህጉን በመጠቀም አስራለች፣ ብዙዎቹ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ መንግስት የዲያስፖራ የቴሌቭዥን ጣብያዎች ላይ አገዳ ጥሏል። የጀርመን ራዲዮ ድምጽ እና የአሜሪካ ራድዮን የመሳሰሉ አለም አቀፍ ራዲዮ ጣብያዎችን ስርችትም ገድቧል፡፡

በሶማሊያ፣ የክልልና የፌዴራል ባለስልጣናት አንዲሁም የታጠቁ ኢስላማዊ ቡድኖች ሚድያ ላይ ያነጣጠሩ ማዋከብ እና ማስፈራራትን ያካተታተ ጥቃቶችን ፈጽመዋል። በዚም ቢያንስ ሁለት ጋዜጠኞች ተገድለዋል። በግንቦት ወር የኬንያ ፍርድ ቤት ፖሊስ ጋዜጠኞችን ለማሰርና ለመክሰስ የተጠቀመው የመረጃና መገናኛ ድርግቶች ኢ-ህገመንግስታዊ አንደነበሩ አዉጆ ነበር።

እ.ኤ.አ. በ 2016ቱ የዩጋንዳ ምርጫ ወቅት የመንግስት ሃላፊዎች እና ፖሊስ ከደርዘን በላይ ጋዜጠኞችን በ ቁጥጥር ስር አውለው ደብድበዋል፡ ባንዳንዶቹ በቀጥታ ስርጭት በታይበት ወቅትም ጭምር ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። በኬንያ አዲስስ የወጣዉን  አወዛጋቢ ህግ በመጠቀም ቢያንስ ስምንት ጋዜጠኞችና ጦማርዎች ታስረው ክስ ተመስርቶባቸዋል። በኢትዮጵያና በዩጋንዳ ባለስልጣናት መንግስት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ በተነሳ ወቅት የኢንተርኔትና ማህበራዊ መገናኛ ብዙህን ለጸጥታ አስፈላጊ ነው በሚል ምክንያት አግደዋል።

በአንድ አንድ ሁኔታዎች መንግስታትና ብሄራዊ ፍርድ ቤቶች የሰብአዊ መብት ጥሰት ሰለባ ለሆኑት ሰዎች ፍትህ የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸቸት በሚያስችል መልኩ አዎንታዊ እርምጃዎች ተወስደዋል። የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ቅሬታን የሚያስተናግድ፣ የእስር ቤቶችንና ህገ-ወጥ ማቆያ ቤቶችን አያያዝ የሚከታተል ብሄራዊ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ህግን ፈርመው አጽድቀዋል። የዩጋንዳ ፍርድ ቤት በድምጽ ብልጫ የእኩል ተጠቃሚነት ኮሚሽን ደንብ ‘’ሰብአዊነት የጎደላቸው እና በህብረተሳቡ ዉስጥ ተቀባይነት የላቸዉም’’ ከሚባሉት ሰዎች ቅሬታን ያለመቀበል መብት በተመለከተ የወጣወን ድንጋጌ ህገ-መንግስታዊ አይደለም በማለት ውሳኔ አሳልፏል።

‘’በምስራቅ አፍሪካ በደህንነት ሽፋን ተያያዥነት ያለቸው በዳይ ግብረ-መልሶች ተስፋፍተዋል። ይህም ቀድሞዉኑ የተገለሉ ማህበረሰቦችን በይበልጥ ገፍቶዋቾዋል’’ ብለዋል ቡርኔት ። ቡርኔት እንዳሉት ‘የአከባቢው መንግስታትና አለማቀፍ ወደጆቻቸው ከትቃት አድራሽ ሀይሎች ጋር ባለመተባበር ተጠያቂነት አንዲሰፍን እና ከመንግስታቱ አስተሳሰብ የተለዩትን አሰተሳሰቦች በመታገስ ላይ ቅድሚያ ሰጥተው አንዲሰሩ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል’፡፡

Your tax deductible gift can help stop human rights violations and save lives around the world.